Skip to Main Content

Amharic

እንኳን ወደ አርሊንግተን ካር ፍሪ ዳይት በሰላም መጡ! በቀላሉ እና ዘና ባለ መንገድ መኪናን የ አለመጠቀም ወይንም መኪናን በጥቂቱ የመጠቀም አኗኗር ዘይቤ ምን ያህል አስደናቂ እንደሆነ የሚያውቁበት፤ መኪናዎን እቤትዎ በመተው ሌሎች ማለትም አውቶቡስ ወይም ባቡር መጠቀም፤ ብስክሌት መንዳት፤ በእግር መጓዝ እንዲሁም መስሪያ ቤት ሳይሄዱ ከቤት ቁጭ ብሎ መስራትና የመሳሰሉትን አማራጮችን ሲወስዱ ምን ያህል ገንዘብዎን እንደሚቆጥቡ፤ ጤናዎን እንደሚያሻሽሉ፤ እንዲሁም አካባቢዎን ከብክለት እንደሚታደጉ የሚገነዘቡበት ፕሮግራም፤


ያለ መኪና አርሊንግተን ወደሚገኘው የኢትዮጵያ ኮሙዩኒቲ (ECDC) እንዴት መሄድ እንደሚቻል ቪዲዮ ይመልከቱ፤

የመጓጓዣ አማራጮች

አርሊንግተን ቨርጂኒያ በአሜሪካ ውስጥ ያለመኪና ለመንቀሳቀስ አመቺ ከሆኑ ምርጥ ቦታዎች አንዱ ነው። ምክንያቱም ሌሎች ብዙ የትራንስፖርት አማራጮች ስላሉ።

ሜትሮ ባቡር በአካባቢው የባቡር አገልግሎት መዋቅር /system/ ነው። በአርሊንግተን 11 የባቡር ጣቢያዎች ሲገኙ በብርቱካናማ ብራማ ሰማያዊ እና ቢጫ መስመሮች የተከፋፈሉ ናቸው። ለተጨማሪ መረጃ በእንግሊዘኛ

ሜትሮ ባስ በዲሲ አካባቢ የባስ አገልግሎት መዋቅር /system/ ሲሆን፤ በአርሊንግተን ዋና ዋና ጎዳናዎች ላይ ከ 25 በላይ በሆኑ መስመሮች የባስ አገልግሎት ይሰጣል። ለተጨማሪ መረጃ በእንግሊዘኛ

ART/ አርሊንግተን ትራንዚት/ የአርሊንግተን ሰፈር ውስጥ የባስ አገልግሎት መዋቅር /system/ ነው። አርሊንግተን ትራንዚት የአርሊንግተንን ከተሞች ያገናኛል፤ ተጠቃሚዎችን ወደ ባቡር ጣቢያ ያደርሳል። ይህ ባስ የሚጠቀመው አካባቢን የማይበክል የተፈጥሮ ጋዝ ነው። ለተጨማሪ መረጃ በእንግሊዘኛ

በአርሊንግተን የእግር ጉዞን የተመቸ ለማድረግ ከተዘረጉ መሰረተ ልማቶች መካከል ሰፋፊ የመንገድ ዳር መንገዶች፤ ረጅም ባለ ብስክሌቶችና እግረኞች በጋራ ሊጠቀሙአቸው የሚችሏቸው መንገዶች፤ ደቂቃን የሚያመላክቱ ማለትም እግረኞች መንገዱን ለማቋረጥ ያላቸውን ቀሪ ግዜ የሚያሳዩ የትራፊክ መብራቶች ዋና ዋናዎቹ ናቸው። ለተጨማሪ መረጃ በእንግሊዘኛ

ብስክሌት መንዳት ጤናማ እና ርካሽ የመጓጓዣ ዘዴ ከመሆኑም በላይ የአካባቢ ጥበቃ ሃላፊነትዎን በሚገባ የሚወጡበት ነው። በአርሊንግተን ካውንቲ ደግሞ ይህን ማድረግ ቀላል ነው። ስለ ብስክሌት መንዳት የበለጠ መረጃ በ BikeArlington.com ላይ ይመልከቱ።

የጋራ ብስክሌቶችን መጠቀም ሌላው የህዝብ መጓጓዣ ዘዴ ነው። በአርሊንግተን ካፒታል ባይክ ሼር (Capital Bike Share) የጋራ ብስክሌት አገልግሎት ሲሆን ይህ ፕሮግራም በአርሊንግተን፤ በዲስትሪክት ኦፍ ኮሎምቢያ፤ በአሌክሳንድሪያ እና ሞንትጐመሪ ካውንቲዎች ጥምር የሚመራ ነው። ለበለጠ መረጃ በእንግሊዘኛ

የጋራ ወይም የኪራይ መኪና በሚያስፈልግዎ ግዜ የሚጠቀሙበትን መኪና በቀላሉ የሚያገኙበት ነው። ይህ ደግሞ የራስዎ የሆነ መኪና ቢኖርዎ የሚያወጡትን ወጪ ማለትም የመኪና መግዣ፤ ኢንሹራንስ፤ ጥገና ያስቀርልዎታል። በአርሊንግተን ለሚገኙ ተጠቃሚዎች የመኪና ክራይ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋሞች Zipcar, Enterprise carshare እና Car2go ናቸው። ለበለጠ መረጃ በእንግሊዘኛ፤

ታክሲ እና ሌሎች ተመሳሳይ አገልግሎት የሚሰጡ የትራንስፖርት ኩባንያዎች (Transportation Network Companies) ለተጠቃሚዎች በተለይም ብስክሌት የእግር መንገድ እንዲሁም መኪናን በጋራ (በየተራ) የመንዳት አማራጮችን ለሚጠቀሙ አጋዥ በመሆን የሚያገለግሉ ናቸው። ለበለጠ መረጃ በእንግሊዘኛ

የአማርኛ ጽሁፎችን ይመልከቱ

PDF, 942 KB, Adobe Reader Required

Arlington’s Car-Free Diet Map (PDF)

በአርሊንግተን የሚገኙ የአውቶቡስ መስመሮችን፤ የብስክሌትና የእግረኛ መሄጃ መንገዶችን፤ የባቡርና የህዝብ(የኪራይ) ብስክሌት ጣቢያዎችን እና ሌሎችን በተቀነባበረ መልኩ የሚያገኙበትን ካርታ ለመመልከት ከታች ያለውን ምስል ወይም ሊንክ ይጫኑ።

 

መንገዶቻችንን በጋራ እንድንጠቀም ፓል(PAL) በመሆን ይተባበሩ

የፓል(PAL) ዘመቻ እያንዳንዱ ሰው በቀላሉ እና በደህና መንገዶችን በጋራ ለመጠቀም እንዴት እንደሚችል የሚያሳውቅ ነው። PAL ሲዘረዘር P-Predictable (አስቀድሞ ወዴትና እንዴት እንደሚሄዱ ማወቅ) A-Alert (ንቁ ወይም ጠንቃቃ) L-Lawful (ህግ አክባሪ) መሆን ነው። ሰዎች PAL ስለመሆን አስፈላጊነት ካወቁ እና መንገድን በጋራ የመጠቀም አስፈላጊነትን ከተገነዘቡ ሁላችንም የመልካምና አስደሳች ጉዞ (የቱንም ያህል ቅርብ ወይም እሩቅ ተጓዥ ብንሆን) ተጠቃሚዎች እንሆናለን። ለተጨማሪ መረጃ በእንግሊዘኛ

መገኛችን፤

አጠቃላይ ኮምዩቲንግ(ጉዞ) የሚመለከቱ ጥያቄዎች፤

ጉዞን በተመለከተ ማንኛውም ጥያቄ ካለዎትና መልሱን ማግኘት ከተቸገሩ የኮሙዩተር ስቶር ሰራተኞችን በስልክ ቁጥር 703-228-RIDE (703-228-7433, TDD: 711) ደውለው መጠየቅ ይችላሉ። አልያም ጥያቄዎን በጽሁፍ ወደ Questions@commuterDirect.com መላክ እና መልስ ማግኘት ይችላሉ። በተጨማሪም አርሊንግተን ውስጥ ከሚገኙት ከአራቱ ሱቆቻችን ወደ አንዱ ጎራ በማለት ወይም ስልክ በመደወል መስተናገድ ይችላሉ።

አርሊንግተን ትራንዚትን የሚመለከቱ ጥያቄዎች

የአርሊንግተን ትራንዚት የደንበኞች አገልግሎትን በስልክ ቁጥር 703-228-RIDE ወይም 703-228-7433 ደውለው በመጠየቅ ይስተናገዱ።

ለአርሊንግተን ትራንዚት (ART) መስራት ይፈልጋሉ? እንግዲያውስ ለበለጠ መረጃ (በእንግሊዘኛ) እዚህ ይጫኑ።

ሜትሮን የሚመለከቱ ጥያቄዎች

ሜትሮ ባቡር፤ ሜትሮ አክሰስ እና ሜትሮ ባስ ከአርሊንግተን ውጪ የሚሰጡትን አገልግሎት በተመለከተ ጥያቄ፤ አስተያየት ወይም ቅሬታ ካለዎ WMATA (Washington Metropolitan Area Transit Authority) ይጠይቁ።

ብስክሌት መንዳትን በተመለከተ ጥያቄዎች

ብስክሌት መንዳትን በተመለከተ አስተያየት፤ ጥቆማ ወይም ቅሬታ ካለዎ በኢሜል አድራሻ info@bikearlington.com ይላኩልን ወይም የ bikearlington.com ድህረ ገፅን ይጎብኙ።

የጋራ (የኪራይ) ብስክሌቶችን የሚመለከቱ ጥያቄዎች

ወደ የደንበኞች አገልግሎት በስልክ ቁጥር 1-877-430-BIKE (2453) በመደወል በእንግሊዘኛ፤ በስፓኒሽ፤ እና ፈረንሳይኛ ቋንቋ ሳምንቱን ሙሉ 24 ሰአት መስተናገድ ይችላሉ። አልያም ጥያቄዎን በኢሜል አድራሻችን customerservice@capitalbikeshare.com በመላክ መልስ ያግኙ።

TDD - አስተማማኝ የስልክ የደንበኞች አገልግሎት የሚያገኙበት ነው፤ መስማት የተሳናቸው እና በደንብ የመስማት ችግር ያለባቸው ሰዎች ከ Virginia, Maryland እና Washington D.C 711 ላይ በመደወል መስተናገድ ይችላሉ።

Arlington Car-Free Diet በአርሊንግተን ካውንቲ ኮምዩተር አገልግሎት (ACCS)፤ በአርሊንግተን ቢሮ እና በቨርጂንያ የአካባቢ ሳይንስ ክፍል ተዘጋጅቶ የቀረበ ነው።

Related Content

Arlington’s Bicycle & Pedestrian Counters

Bikes counted

View Counter Data
110 Trail
399
14th Street Bridge
1203
Arlington Mill Trail
284
Ballston Connector
0
Bluemont Connector
248
CC Connector
348
Clarendon EB bike lane
250
Custis Bon Air Park
825
Custis Rosslyn
707
Eads NB
40
Eads SB
69
Fairfax EB bike lane
113
Fairfax WB
122
Joyce St NB
34
Joyce St SB
0
Key Bridge East
1148
Key Bridge West
870
Military NB bike lane
26
Military SB bike lane
19
MVT Airport South
1535
Quincy NB bike lane
92
Quincy SB bike lane
86
Roosevelt Bridge
297
Rosslyn Bikeometer
843
TR Island Bridge
783
WOD Bon Air Park
0
WOD Bon Air West
1284
WOD Columbia Pike
1000
Wilson WB bike lane
179

Peds counted

View Counter Data
110 Trail
952
14th Street Bridge
755
Arlington Mill Trail
774
Ballston Connector
0
Bluemont Connector
1335
CC Connector
731
Custis Bon Air Park
980
Custis Rosslyn
700
Eads NB
0
Eads SB
0
Fairfax WB
0
Joyce St NB
53
Joyce St SB
0
Key Bridge East
3776
Key Bridge West
698
MVT Airport South
934
Roosevelt Bridge
397
TR Island Bridge
1811
WOD Bon Air Park
0
WOD Bon Air West
0
WOD Columbia Pike
1125

All counters, YTD

View Counter Data
Year to Date
6827924